መጋቢት 27 2017 - ‘’የፌዴራል ህጎች በክልል ደረጃ የተቀራረበ አተረጓጎም እንዲኖራቸው በትኩረት መስራት ይገባል’’ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕ/ት ቴዎድሮስ ምህረት
- sheger1021fm
- Apr 5
- 1 min read
‘’የፌዴራል ህጎች በክልል ደረጃ የተቀራረበ አተረጓጎም እንዲኖራቸው በትኩረት መስራት ይገባል’’ ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ተናገሩ።
አቶ ቴዎድሮስ እንዳሉት ህጎቹ በክልል ደረጃ በተቀራረበ ደረጃ እየተተረጎሙ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ በየጊዜው መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና ውጤቱን መሰረት በማድረግ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ።
አተረጓገሞቹ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በዚህ መንገድ ማረም ችግሮችን ከምንጫቸው ለመፍታት ያስችላል ነው ያሉት።

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ የሁሉም ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች ያሉበት ነው።
በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኘ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክርም አቶ ቴዎድሮስ በመድረኩ ላይ ሲናገሩ ሠምተናል።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Commentaires