ፍርድ ቤቶች አካባቢ ያለው አሰራር ለማዘመን እና መዝገቦች እንዳይጠፉ ለማድረግ የዲጂታል አገልግሎት እየተተገበረ መሆኑን ተነገረ።
አሰራሮች ማዘመን ከተቻለ ማህበረሰቡ ባለበት ሆኖ ፍትህ እንዲያገኝ ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ‘’በፍርድ ቤቶች አካባቢ የዲጂታል አሰራር አየተዘረጋ ነው’’ ብለዋል።
‘’ፍርድ ቤቶች የተሻለ አሰራር ለመስጠት እንዲችሉ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል’’ የተባለ ሲሆን ‘’የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ፍርድ ቤቶች ነፃ ሆነው ፍትህ እንዲያሰፍኑ ይረዳቸዋል’’ ተብሏል።
አርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ድምፅን ወደ ፅሁፍ የመቀየር ስራ እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን በፍርድ ቤት ያለው አሰራር ለሁሉም ነፃ እና ግልፅ በሆነ መንገድ እንዲከወን እየተሰራ ነው ሲባል ሰምተናል።
የጀስትስ ፎር ኦል ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ ‘’ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የፍትህ ሥርዓቱ እየፈተነው ነው ፣ ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ ይታፈናሉ የፍትህ ረገጣ ይታያል ህዝቡ አሁን ላይ ፍትህን ይፈልጋል’’ ብለዋል።
‘’የፍትህ ሥርዓቱ ለማዘመን የሚደረግ ጥናት ካለ እናግዛለን’’ ያሉ ሲሆን ‘’በፍትህ ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ፍትህን እንደ ሀገር ለማስፈን በጋራ መስራት አለባቸው’’ ሲሉ አሳስበዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትህ ሥርዓቱን ለማዘመን እንዲያስችል ፍኖተ ካርት ያዘጋጀ ሲሆን ክልሎችና የከተማ አስተዳድሮችም ተመሳሳይ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተዋል መባሉንም ሰምተናል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments