በኢትዮጵያ ከተለመደውና ዋስትናን መሠረት ካደረገ የብድር አገልግሎት ውጪ ባሉ አማራጮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ ሲነገር እንደሠማነው ለግል የፈጠራ ውጤቶች፣ ለባለቤትነት መብት ወይም ኮፒ ራይት፣ ለንግድ ምልክቶች እና ለንግድ ሚስጥሮች ብድር የማቅረብ አሰራር በኢትዮጵያ ሊለመድ ይገባል።
ለአዕምሯዊ ፈጠራ ውጤቶች የሚሰጥ ብድር የስራ ዕድል እንዲሰፋ ያግዛል ነው የተባለው።
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ ችግር የሚያቃልል ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ለተጨማሪ ፈጠራ ሰዎችን እንደሚያነሳሳም የውይይቱ አዘጋጅ የሆነው የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፀሃፊ አቶ ስዩም ጫኔ ተናግረዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comentários