የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ለማህበረሰቡ ለማድረስ 2 ሚሊዮን ብር አውጥቼ የገነባሁት የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ ሲል ቢጅ አይ ሜታ አቦ ፋብሪካ ተናገረ፡፡
በሰበታ ከተማ ዋጅቱ ኢሬቻ አካባቢ በመብራት እጦት ምክንያት ነዋሪው ተቸግሮ መቆየቱን በማየት የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር በመትከል የአካባቢው ማህበረሰብ የመብራት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉን ኩባንያው አስረድቷል፡፡
ስራውን ለመከወን የሶስት ወር ጊዜ የፈጀ ሲሆን አገልግሎቱ ከ70 በላይ አባውራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም በፕሮጀክቱ ማስመረቂያ መረሀ ግብር ላይ ሲነገር ሰምተናል።
ቢጅአይ ሜታ አቦ ፋብሪካ ሌላኛው ለማህበረሰቡ ክፍት ያደረገው አገልግሎት በከተማዋ በሚገኝ ዲማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የታካሚዎች ማረፊያ ቦታ ነው።
በሆስፒታሉ ውስጥ የተገነባው የታካሚዎች ማረፊያ 7.2 ሚሊየን ብር ወጭ እንደተደረገበት የተናገሩት የቢጅአይ ፋብሪካ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በሀይሉ አየለ ግንባታው የ3 ወር ጊዜ ፈጅቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ብለዋል።
በ7.2 ሚሊዮን ብር ተገነባ የተባለው የታካሚዎች ማረፊያ በአንድ ጊዜ ከ240 በላይ ተገልጋዮችን እንደሚያስተናግድ ተነግሮለታል።
ቢጅአይ ሜታ አቦ ፋብሪካ ለ700 አባወራዎችን የዓመት የህክምና ወጭያቸውን ለመሸፈን እና የጤና መድን ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን የ800 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጌአለሁ ብሏል።
ድርጅቱ በአጠቃላይ ሰርቶ ለማህበረሰቡ ያስረከበው ፕሮጀክት 10 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን ሲከውን መቆየቱን እና ከዚህ በኃላም ተመሳሳይ ስራዎችን ለመከወን ውጥን መያዙን ሲናገሩ ሰምተናል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments