የንግድና ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ፣ የናይጄሪያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ እና ኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ ከኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ድርሻ መግዛታቸው ተሰማ፡፡
ሶስቱ ኩባንያዎች የ250 ሚሊዮን ብር ድርሻ መግዛታቸው ተነግሯል፡፡
ይህ የተሰማው ዛሬ የሰነደ ሙዓለ ገበያ በገበያው ወደ ስራ ለመግባት 1.5 ቢሊየን ብር ወይም 26.6 ሚሊየን ዶላር ካፒታል መሰብሰቡን በተናገረበት ግዜ ነው፡፡
ገበያው ለመሳብ ካቀደው ካፒታል 11.07 ሚሊየን ዶላር በ 240 በመቶ በልጦ 26.6 ቢሊየን ዶላር ሰብስቧል ተብሏል፡፡
በጠቅላላው በዚህ ገበያ 48 የሐገር ቤትና የውጭ ተቋሞች ተሳትፈዋል ሲባል ሰምተናል፡፡
በገበያው ተሳትፈዋል የተባሉት ተቋሞች ከፋይናንስ ዘርፍ ውጭ ያሉም እንዳሉ ሰምተናል፡፡
16 ባንኮች፣ 12 የኢንሹራንስ ድርጅቶች እና 17 በአምራችና በአገልግሎት ሰጭ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡
የኢትዮዽያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል በኢትዮዽያ የካፒታል ገበያ ዕድሎች ላይ ባለሀብቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን እውቅና ሰጥተው በተለይ የውጭ ግዙፍ ኩባንያዎች መሳተፋቸው ስትራቴጅካዊ ኢንቨስትመንቶች የቴክኒካል እውቀት ሽግግርና ጥሩ ልማድ ፈጥሯል ብለዋል፡፡
የፋይናን አካታችነትን ለማካተትና ለአብዛኛው ህዝብ ጥሪት ለመፍጠር የተቋቋመው የኢትዮዽያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመጭዎቹ ወራት ወደ ገበያው ለመግባት ወሳኝ የሆኑ ተግባራት እያከናወንኩ ነው ብሏል፡፡
ገበያው ጥቅምት 2016 ዓ.ም መቋቋሙ ይታወቃል፡፡
በኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል 25 በመቶ የተፈቀደ ካፒታል ድርሻ ሲይዝ 75 በመቶ የግል ዘርፍ ድርሻ እንደሚይዝም ይታወቃል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments