top of page

መጋቢት 26፣2016 - የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ አምባሳደር ለምክክር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ተሰማ

የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ አምባሳደር ለምክክር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ተሰማ፡፡

 

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሐመድ ዋሬ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ እና እንዲመካከሩ የተደረገው ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተዘግቧል፡፡

 

ሶማሊያ፣ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሀገሯ እንዲወጡ ከመወሰኗ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ ሀርጌሣ እና በፑንትላንድ ጋሮዌ ያሏት ቆንስላ ፅ/ቤቶችን እንደዘጉ ወስናለች፡፡

 

በሁለቱ ቆንስላ ፅ/ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ሀገራቱን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ እና ቆንስላ ጽ/ቤቶቹም እንዲዘጉ መወሰኑንን ጋሮዌ ኦንላየን ፅፏል፡፡

 

ይህንን ትዕዛዝ በማይቀበሉት ላይም በአለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ህግ መሰረት ሀገሪቱ ተጨማሪ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች፡፡

 

ውሳኔው የሚፀናው  የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ም/ቤት ሲያፀድቀው እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፈረሙበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

 

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንዲሁም በሀርጌሣ እና ጋሮዌ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች እንዲዘጉ ተወስኗል ስተባለው ጉዳይ ሸገር የጠየቃቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ መረጃው እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ባለፈው ታህሳስ 22/2016 በአዲስ አበባ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተከትሎ ሶማሊያ በሉዓላዊነቴ ተነካ ከፍተኛ ቁጣ ማሰማቷ ይታወሳል፡፡

 

በትላንትናው እለት ደግሞ ኢትዮጵያ እና  የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት አካል ሆና የቆየችው  ፑንትላንድ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶችን ለማሻሻል መስማማታቸው ተነግሯል፡፡

 

ፑንትላንድ ከእንግዲህ ከሞቃዲሾ ጋር ያለኝን ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት አቋርጫለሁ ማለቷ ይታወሳል፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በፑንትላንድ የገንዘብ ሚኒስትር  መሀመድ ፋራህ መሀመድ የተመራ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድንን  በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

 

ኢትዮጵያ በተለይ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ለፑንትላንድ እያደረገች ላለው ድጋፍ ልዑካን ቡድኑ ምስጋና አቅርቧል።

 

ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላት ግንኙነት  ለሚኖራት ግንኙነት ቁርጠኛ መሆኗን አምባሳደር ምስጋኑ አስረድተዋል።

 

ለፌዴራል መንግስቱ እውቅና የነፈገው የፑንትላንድ አስተዳደር ከእንገዲህ ራሴን የቻልኩ ነፃ መንግስት ነኝ ብሏል፡

 

ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comments


bottom of page