top of page

መጋቢት 26፣2016 - ''ከዚህ በፊት ቅርስ ናቸው ብዬ የመዘገብኳቸው እንደገና ሳጣራ ቅርስ ሳይሆኑ አግኝቻቸዋለሁ'' የቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን

ለመልሶ ግንባታ ቤት ፈረሳው በበዛበት ፒያሣ እና ዙሪያዋ ቅርስ ናቸው ተብለው ተመዝግበው ከነበሩት ቤቶችና ህንፃዎች አብዛኛዎቹ ፈርሰዋል፡፡


ከሁለት እና ሶስት ዓመት በፊት በቅርስነት ተመዝግበው ከነበሩት 147 ቤቶች ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው የቅርስነትን መስፈርት የሚሟሉት ተብሏል፡፡


የቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በፊት ቅርስ ናቸው ብዬ የመዘገብኳቸው አሁን ላይ እንደገና ሳጣራ ቅርስ ሳይሆኑ አግኝቻቸዋለሁ ሲል ተናግሯል፡፡

 

ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ‘’አንድ ህንፃ እድሜው ብቻ ቅርስ ሊያስብለው አይችልም’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡


‘’2 መቶ ሺህ ሰዎችን የሚጠቅም ፕሮጀክት ለ90 ዓመት ህንፃ ብለን ይቁም ማለት አንችልም’’ ያሉት ዳይሬክተሩ ‘’እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አለም፤ ልማት ሲሰራ የተወሰኑ ቅርሶችን ይጎዳል’’ ብለዋል፡፡


ይሁን እንጂ ቅርስ እና ልማት አብሮ ለማስኬድ፤ ከከተማ አስተዳደሩ በጋራ እየከውንን ነው ብለዋል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comments


bottom of page