top of page

መጋቢት 25 2017 - አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 3
  • 1 min read

አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡን ተናገረ።


ባንኩ ለ4ተኛ ጊዜ ከ36 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች ውስጥ ከኢትዮጵያ ብቸኛ ሆኜ ተመርጫለሁ ብሏል።


ግሎባል ፋይናንስ ለ32ተኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮች ዝርዝርን ይፋ ማድረጉን አስመልክቶ ነው፤ ከአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ባንኮች ተብለው ከተመረጡ 36 ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን የተናገረው።


በዓመቱ ውስጥ ያስመዘገቡት የትርፍና የጠቅላላ የሀብት እድገት መጠን ባንኮቹ የተመረጡበት ዋና መስፈርቶች ናቸው ተብሏል።

በጠቅላላ ሀብት ዕድገትና በሀብት መጠን፣ በአጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ እድገትና ዓመታዊ ትርፍ፣ በብድር አቅርቦት፣ በተከፈለ ካፒታል ዕድገትና በትርፍ ድርሻ ክፍፍል ነው ባንኩ ከምርጥ ባንኮች አንዱ ሆኖ ሊመረጥ የቻለው ተብሏል።


በሌላ በኩል ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የዕድገት መለኪያዎች ማለትም በደንበኛ ብዛትና በገበያ ድርሻ እድገት፣ በብራንድ ግንባታ፣ በቅርንጫፍ ስርጭት፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስፋትና በቀልጣፋ አገልግሎት እና በሌሎችም ዘርፎች አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ምርጥ ባንክ ሆኖ ለአራተኛ ጊዜ መመረጥ መቻሉን ተናግሯል።


በምርጫው አሸናፊ ለሆኑ ባንኮች የሚሰጠው የእውቅና ሽልማት የአለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የአለም ባንክ በአሜሪካ በመጪው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በሚያደርጉት ዓመታዊ የጋራ ጉባኤ ላይ ነው ተብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page