top of page

መጋቢት 25 2017 - ''በጤና ተቋማት የሚከፈሉ ክፍያዎች በዲጂታል መልኩ እንዲሆኑ እየሰራሁ ነው'' ጤና ሚኒስቴር

  • sheger1021fm
  • Apr 3
  • 1 min read

በመንግስት የጤና ተቋማት የሚከፈሉ ክፍያዎች በሙሉ በዲጂታል መልኩ እንዲሆኑ በርትቼ እየሰራሁ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማት የክፍያ መፈጸሚያ ስርዓታቸው በዲጂታል እንዲሆን ይገደዳሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡


ይህ አሰራር በተለይ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ስራው ተጀምሯል ተብሏል፡፡


ይህንን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ስራ አስፈጻሚ ገመቺስ መልካሙ ናቸው፡፡


መሪ ስራ አስፈጻሚው በአሁኑ ጊዜ በርካታ የግብይት ስርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተለወጡ መምጣታቸውን ጠቅሰው የጤናውም ዘርፍ የዚህ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለውናል፡፡

ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ሲሄዱ የሞባይል ስልካቸውን በመጠቀም ክፍያ እንዲፈፅሙ ይደረጋል፤ ይህ ደግሞ ለግልጸኝነት እና ለተጠያቂነት ያግዛልም ብለዋል፡፡


በተለይ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች እና ዘመንኛ ስልኮችን የማይጠቀሙ ሰዎች ክፍያዎችን በዲጂታል መንገድ ለመፈፀም ሊቸገሩ ይችላሉ ለነዚሀም የተለያዩ አማራጮችን እየተፈለጉ ነው ብለውናል፡፡


በገጠር አካባቢዎች ስርዓቱ ለመተግበር እንደሙከራ የተለዩ ወረዳዎች እንዳሉም አቶ ገመቺስ ነግረውናል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page