መጋቢት 25፣2016 - የወጪ ንግድ ገቢ ከአምናው ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል ተባለ
- sheger1021fm
- Apr 3, 2024
- 1 min read
ኢትዮጵያ ባለፉት 8 ወራት ከወጪ ንግድ ያገኘችው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል ተባለ፡፡
በጊዜው ከወጪ ንግድ ለማግኘት የተቻለው የእቅዱን 69 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ8 ወር የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡
ሪፖርቱን በንባብ ለእንደራሴዎቹ ያቀረቡት የንግድ ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ናቸው፡፡
ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው በ 8 ወር ዉስጥ ከወጪ ንግድ 3.14 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማግኝት የተቻለዉ ግን 2.16 ቢሊዮን ዶላር ነው ተብሏል፡፡
ከባለፈው አመት የ8 ወር የስራ አፈፃፀም 2.3 ቢሊየን ዶላር ተገኝቶ ነበር ዘንድሮ ግን በ8 ወር ውስጥ ማግኘት የተቻለው 2.1 ቢሊየን ዶላር ነው ተብሏል፡፡

የዘንድሮ አመት የ8 ወር የስራ አፈፃፀም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ እንዳለው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ አስረድተዋል፡፡
በዚህም ድርሻቸው ግብርና 73.1 ማኒፋክቸሪንግ 50.9 በመቶ ማዕድን 53.9 በመቶ እና ኤሌክትሪክ 69 በመቶ ድርሻ አላቸው ተብሏል፡፡
ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው በርካታ ችግሮች ቢኖሩም የበረቱት ግን የህግ ወጥ ንግድና የሰላም እጦት እንደሆነ አብራርቷል፡፡
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት አመቱ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን አግኝቻለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡
ከዚህ በፊት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለ3 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የቁም እንስሳት ግብይትም በበጀት አመቱ ተጀምሯል ብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments