የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መደገፉን እንደሚበረታበት አረጋገጠ።
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ላሉ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከ350 ሚሊየን ዶላር በላይ ብድር ቀደም ብሎ ሰጥቷል።
ከባንኩ በተገኘ ብደር እየተደገፉ ያሉ እነዚህ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ያለመ የመስክ ጉብኝት ትናንት ተካሂዷል።
የመስክ ጉብኘቱ የዓለም ባንክ ቡድን ምክትል ፕሬዘዳንት ሊሳ ሮሰን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና ሌሎች ባለስልጣናት የተሳተፉበት ነው ተብሏል፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ ያሉበት ደረጃ፣ የፈጠሩት የስራ ዕድል እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦቸው በምልከታው ወቅት መገመገሙን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አበባ ታመነ ነግረውናል።
የዓለም ባንክ ቡድን ምክትል ፕሬዘዳንት ሊሳ ሮሰን የተመለከቷቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች፤ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተጣጣመ ስራ እየሰሩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው የመስክ ምልከታው የኢንዱስትሪዎችን እንቀስቃሴ በማየት ፤
የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ያገዘ ነው ብለዋል።
ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ባለፉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ ለሚገኙ አአምራቶች ኢንዱሰትሪዎች የመስሪያ ማሽንና የስራ ማስኬጃ ያለምንም ማስያዣ በማቅረብ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለባቸው ንጉሴ ናቸው።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
コメント