top of page

መጋቢት 25፣2016 - አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ለማገዝ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናገረ

አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ለማገዝ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናገረ፡፡


የድርጀቱ ባልደረቦች በኢትዮጵያ ለ13 ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል፡፡


በአልቫሮ ፕሪስ የተመራው የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አባላት የጉብኝታቸው አላማ IMF የኢትዮያን የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም በሚደግፉበት ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡


ከጉብኝቱ መጠናቀቅ በኋላ አጭር መግለጫ ያወጣው IMF የተደረገው ውይይት ከዚህ በፊት የተደረጉ ውይይቶች ተከታይ እንዲሆን አስረድቷል፡፡


በዚህም IMF እንዴት ባለ ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መደገፍ ይችላል በሚለው ላይ ተጠቃሚ ለውጥ የታየበት ምክክር ተደርጓል ብሏል፡፡


ይህ በውይይቱ ወቅት ታይቷል ስለተባለው ጠቃሚ ለውጥ ግን ድርጅቱ ያለው ነገር የለም፡፡


የኢትዮጵያ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ያወጣው መግለጫ አልታይም፡፡


ውይይቱ በ IMF እና የአለም ባንክ የፀደይ ወቅት ምክክር ወቅትም ይቀጥላል ተብሏል፡፡


ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comentarios


bottom of page