መጋቢት 24 2017 በአዲስ አበባ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት፤ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ ተፈቀደ
- sheger1021fm
- Apr 2
- 1 min read
ከዛሬ መጋቢት 24 2017 ጀምሮ፤ በአዲስ አበባ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ ተፈቀደ።
የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው እና በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ መፈቀዱን የተናገረው የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ በአቅራቢያ መንጃ ፈቃድ የማደስ ጥያቄ ዓመታትን የተሻገረ ነበረ ብሏል።
አገልግልሎቱን የፈለገ ማንኛውም ሰው ፋይሉ ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ፤ በሚቀርበው ቅርንጫፍ፤ የጤና ምርመራ ሰርተፊኬት በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ማግኘት ይችላል ተብሏል።
Comments