top of page

መጋቢት 23 2017 - ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው የ50 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 1 ዶላር ካለፈው ጨረታ በ4 ብር ቅናሽ ባለው ዋጋ ተሸጧል

  • sheger1021fm
  • Apr 1
  • 1 min read

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው የ50 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 1 ዶላር ካለፈው ጨረታ በ4 ብር ቅናሽ ባለው ዋጋ ተሸጧል፡፡


በጨረታው የተሳተፉ ባንኮች ቁጥር በ15 ቀንሷል፡፡


ብሔራዊ ባንክ በዛሬው እለት ያወጣው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በአማካኝ 1 ዶላር 131.7 ብር ተሽጧል፡፡


ከወር በፊት በነበረው የ60 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ አንድ ዶላር እስከ 141 ብር ባለው ዋጋ መሸጡ ይታወሳል፡፡


ባንኩ በዛሬው እለት ለ3ኛ ጊዜ ያቀረበው የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ 12 ባንኮች እንደተሳተፉበት የተነገረ ሲሆን የ1 ዶላር አማካኝ ዋጋ 131.7 ብር እንደሆነ ከባንኩ መግለጫ ተመልክተናል፡፡


ለሁለተኛ ዙር በየካቲት አጋማሽ ላይ ለጨረታ ቀርቦ የነበረው የ60 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ጨረታ 1 የአሜሪካ ዶላር በ135.6 ብር ተሽጦ ነበር፡፡


ይህ ለ3ኛ ጊዜ የቀረበው የውጪ ምንዛሪ ጨረታ ግን ከሁለተኛው ጨረታ የ4 ብር ቅናሽ አሳይቷል፡፡


በጨረታው የተወዳደሩ ባንኮች ቁጥር ባለፈው 27 የነበረ ሲሆን አሁን ከእጥፍ በታች ቀንሷል፡፡


ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ጨረታን በየ15 ቀኑ ከዚህ በኋላ እንደሚያወጣ መናገሩ ይታወሳል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page