መጋቢት 23 2017 - በአማራ ክልል ቅዳሜ ለሚደረገው የምክክር ምዕራፍ ተሳታፊዎች ከመላው የክልሉ አካባቢዎች በሰላም ወደ ባህርዳር እንዲገቡ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Apr 1
- 1 min read
በአማራ ክልል ቅዳሜ ለሚደረገው የምክክር ምዕራፍ ተሳታፊዎች ከመላው የክልሉ አካባቢዎች በሰላም ወደ ባህርዳር እንዲገቡ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
ይህን ያለው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው፡፡
ኮሚሽኑ የ #አማራ_ክልል የምክክር ምዕራፍ በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር ተናግሯል፡፡
ለዚህም ምክርክር የሚስፈልጉ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ነግረውናል፡፡
በግጭት ውስጥ ባለው የአማራ ክልል ምክር ለማደርግ ከወረዳ የተወከሉ ተሳተፊዎች ወደ ምክክሩ ስፍራ ባህር ዳር በሰላም እንዲመጡ ከክልሉ መንግስት ጋር እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በአማራ ክልል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰላም ሳይሰፍን፣ ግጭት ሳይቆም፣ ታጣቂዎች ሳይሳተፉ እና የፖለቲካ እስረኞች ሳይፈቱ ምክክር ማካሄድ እንዳይጀምር ከጀመረም ወጤቱ የሚጠበቀው ላይሆን እንደሚችል በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ይህ ጥያቄ ምን መልስ አግኝቶ ነው ስራ የተጀመረው? ኮሚሽኑን ጠይቀናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments