መጋቢት 22 2017 - የራሱን የኢኮኖሚ አቅም የሚያዳብር ለሌሎችም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሊሰራ የሚችል ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤምኤስአይ ኢትዮጵያ ተናገረ
- sheger1021fm
- Mar 31
- 1 min read
የራሱን የኢኮኖሚ አቅም የሚያዳብር ለሌሎችም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሊሰራ የሚችል ኢንቨስትመንት ውስጥ መሰማራቱን ኤምኤስአይ ኢትዮጵያ ( #MSI ) ተናገረ፡፡
ግብረ ሰናይ ድርጅት የሆነው ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ከለጋሾች ጥገኝነት ለመላቀቅ ያግዙኛል ባላቸውንና ወጪያቸውን በራሳቸው በሚሸፍኑ ሁለት የእናቶችና ህፃናት የህክምና ማዕከላት በወር ከ9ሺ በላይ ደምበኞችን እያስተናገደ መሆኑን ነግሮናል፡፡
በኢንቨስትመንት ውስጥ ልንሰማራ የቻልነው ባለፉት 6ዓመታት ስንሰራ በቆየንበት የሶሻል ቢዝነስ ሞዴል ነው የሚለው ድርጅቱ በግብረሰናይ ድርጅቶች ዘንድ ባልተለመደ አኳኋን የራሳቸውን ገቢ በሚያመነጩ በተለይም ፒያሳ አካባቢ ባለው አራዳ ቅርጫፍና 22 ቅርጫፍ የጤና ማዕከሉ ድርጅቶቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እዩልኝ ብሏል፡፡
የስነ ተዋልዶ ጤና፣የቅድመ እና ድህረ ወሊድ አገልግሎትና የህፃናት ህክምና የሚሰጥባቸው ማዕከላቱ አሁን ያለውን የህክምና ዋጋ ውድነት ታሳቢ በማድረግ በመንግስት የጤና ተቋማት ከሚከፈለው ከፍ ባለ፤ በግል የጤና ተቋማት ከሚጠየቀው በቀነሰ ተመጣጣኝ በሚለው ዋጋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ኤም ኤስ አይ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር አበበ ሽብሩ ጠቅሰዋል፡፡
ይህ የቢዝነስ ሞዴል ከትርፍ ይልቅ ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት የራስን ገቢ ማመንጨት ላይ ያተኩራል የሚሉት ሃላፊው ከእነዚህም በተጨማሪ በመላው ሃገሪቱ ባሉት 21 መሰል ማዕከላት በሚሰጠው አገልግሎት ከሚያገኘው ገቢ ባለፉት ዓመታት 82 ሚሊዮን ብር መለንግስት ታክስ መክፈሉንም አንስተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት አላማ ጋር በሚገናኝ የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ መደረጉ እኛም በቢዝነስ ስራ ላይ እንድንሰማራ አግዞናል ሲሉ አስረድተዋል ሃላፊው ዶ/ር አበበ፡፡
ይህንን ኢንቨስትመንት በማስፋትና በገቢ ራስን በመቻል ከለጋሾች ተፅዕኖ ለመላቀቅ ውጥን አለኝ የሚለው ድርጅቱ በዓመት ለ2 ሚሊዮን እናቶችና ህፃናት የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ሲናገር ሰምተናል፡፡
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments