top of page

መጋቢት 22 2017 - በኢትዮጵያ ከግጭት መውጫ መንገድ ነው ያለውን አማራጭ ሃሳብ እንዳቀረበ የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ጥምረት ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Mar 31
  • 1 min read

በኢትዮጵያ እዚህም እዚያም ካለው ግጭት መውጫ መንገድ ነው ያለውን አማራጭ ሃሳብ እንዳቀረበ የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ጥምረት ተናገረ፡፡


አማራጭ ነው ያለውን ሃሳብ ይዞ ፖለቲከኞችን የማነጋገር ውጥን እንዳለውም ሰምተናል፡፡


በበጎ ፍቃደኝነት የተሰባሰቡ እናቶችን የያዘው ጥምረቱ ኢትዮጵያን ከአንዱ ችግሯ ወደ ሌላው እያሸጋገረ በቅጭት አዙሪት ውስጥ ያኖራት ማህበረሰቡ አሳሳቢ የሆነ የሞራል ውድቀት ውስጥ በመሆኑ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡


ከገባንበት የሞራው ውድቀት መውጫው በተለይ በሁሉም ቤተ እምነት ውስጥ ያለው በጎ የሆነ የሞራል አስተምህሮ ተከታይ በሆነው አብዛኛው ኢትዮጵያው ውስጥ ማስረፅ እንደሆነም ነግረውናል፡፡


ይህንን የማድረግ ሃላፊነት ያለባቸው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ተከታይ የሆነባቸው 4ቱ ቤተ እምነቶች ናቸው የሚለው ጥምረቱ የእነዚህ ቤተ እምነት አባቶች ከመጠፋፋት ይልቅ ወደ ሰላም የሚያመጣ የጋራ የሆነ የፆም፣የፀሎትና የንሰሃ አዋጅ እንዲያውጁ ጠይቀዋል፡፡ወ/ሮ መዓዛ በቀለ የጥምረቱ አስተባባሪ ናቸው፡፡


ሰላምን ለማምጣት በሃይማኖቶች በር መግባት የተሻለ ቢሆንም የሰላም እጦቱ ዋንኛው መነሻ ፖለቲካው እንደመኖኑ እንደ ሃይማኖት አባቶች ሁሉ ከመሪዎች ጀምሮ ያሉ ፖለቲከኞችን ለማነጋገር ውጥን ካላችሁ ብለን ለጠየቅናቸው፤ ፖለቶከኞቹን በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር እንፈልጋለን ግን ይህንን የምናደርገው በጥንቃቄ ነው ብለውናል፡፡


የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ጥምረት ይህንን ሃሳቡን ለእምነት አባቶቹ ባለፈው ጥር ወር አቅርቦ ምላሻቸውን እየተጠባበቀ እንደሆነና ይህንን ጥሪ ለማቅረብ የተገደደው ኢትዮጵያን ካለችበት የግጭት አዙሪት ሊያስወጣ የሚችል የጠነከረ ተስፋ በማጣታቸው መሆኑንም ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..




ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page