top of page

መጋቢት 21፣2016 - ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰማ፡፡


ከሰኞ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ወይይት ይደረጋል፤ በማጠቃለያው ቀንም ለፓርቲ መሪዎቹ ስልጠና ይሰጣል ተብሏል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ አዲስ አበባ ከክልል ያልጠሯቸው የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አዲስ አበባ መድረሳቸውን ከምንጮቻችን ሰምተናል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለውይይት የጠሯቸው የሀገር አቀፍ እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲ የበላይ ሀላፊዎችን ነው ተብሏል፡፡


ለሀገር አቀፍ ፓርቲ ሊቀመንበር ምክትል እና የፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም ሶስት የስራ አስፈፃሚ አባላትን በድምሩ ስድስት ሰዎችን ለክልል ፓርቲዎች ደግሞ ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና የፅ/ቤት ሀላፊ በድምሩ ሶስት ሰዎች ናቸው የተጠሩት ተብሏል፡፡


ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ግብዣ ኮከስ በሚል የተመሰረተው እና 13 አባላትን የያዘው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰብ ጥሪውን አለመቀበሉንም ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡


የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments


bottom of page