top of page

መጋቢት 20፣2016 - የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ውስጥ 34 ከመቶ የሚይዘው የለስላሳና የውሀ መጠጥ መያዣ ኮዳ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Mar 29, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታየው የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ውስጥ 34 ከመቶ የሚይዘው የለስላሳ መጠጥና የውሀ መጠጥ መያዣ ኮዳ ነው ተባለ።

 

ከዚህ ባለፈ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ችግር ምክንያት 38 ሺህ ሰዎች በየዓመቱ ሕይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።

 

ይህ የተባለው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለ6 ወር ተግባራዊ ለማድረግ ይፋ ባደረገው የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ ላይ ነው።

 

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በ6 ወራቶቹ ውስጥ የፕላስቲክ፣ የአየር፣ የውሃ፣ የድምፅ  እና የአፈር ብክለትን ለመከላከል እና ግንዛቤ መፍጠር ስራ ይሰራል ተብሏል።

 



ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በአየር ለውጥ ምክንያት ድርቅ እያጥቃት መሆኑን አስታውሰዋል።

 

‘’ይህንን ለመከላከል አካባቢን ከብክለት መከላከል ያስፈልጋል’’ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘’መንግስት የአየን ንብረት ለውጥና የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየሰራ ነው’’ ሲሉ ሰምተናቸዋል።

 

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ሌሊሴ ነሚ ‘’በመጪዎቹ በ6 ወራት ውስጥ የአፈር፣ አየር ፣የውሃ የድምፅ የብፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከልና ሰዎችን በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ይሰራል’’ ብለዋል።

 

የፕላስቲኮች ውጤቶች 46 ከመቶ፣ የለስላሳ እና የውሃ ኮዳዎች 34 ከመቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚከሰተው የፕላስቲክ ብክለት ድረሻ  ይይዛሉ ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

 

አብዛኞቹ ሆቴሎች ፍሳሽ ቆሻሻ የሚለቁት ወደ ወንዞች ነው የተባለ ሲሆን ይህንን ለማስተካከል ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ መሆኑን ሰምተናል።

 



የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራሏ ከአየር ብክለት ጋር በትያያዘ በዓመት 38 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን  ያጣሉ ብለዋል።

 

ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ የተደረጉ ጥናቶች በጥራት አልተሰሩም የተባለ ሲሆን በ6ወር ውስጥ ባለስልጣኑ ይህንን በተመለከተ ጥናት አደርጋለሁ ብሏል።

 

የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ይደረጋል የተባለው ንቅናቄ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደሚካሄድ፣ ከውሃ ኮዳዎች ጀምሮ የፕለስቲክ ምርቶች መቀነስ አና መልሶ መጠቀም እንዲሁም የአካባቢ ብክለት የሌላቸው ምርቶችን መጠቀም ለማበረታታት ይሰራል መባሉን ሰምተናል።

 

 

በረከት አካሉ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page