top of page

መጋቢት 20፣2016 - የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ያጋጠመው በማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተከሰተ ችግር እንደሆነ ተነገረ

ትናንት ለተወሰኑ ሰዓታት በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ያጋጠመው በማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተከሰተ ችግር እንደሆነ ተነገረ፡፡


በማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የተከሰተው ችግር ከማመንጫዎች የወጣውን ኤሌክትሪክ ወደ ብሄራዊ መቆጣጠሪያ ማዕከል ወይም ግሪድ ማስገባት እንዳይቻል አድርጎ ነበር ተብሏል።


የተፈጠረውን ችግር የተቋሙ ሞያተኞች ሁለት ሰአት ባልሞላ ጊዜ አስተካክለው ሃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በሙሉ ዳግም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ማድረጋቸውንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል።


የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከትናንት ምሽት አንድ ሰአት ጀምሮ ዳግም ሃይል ማግኘት መጀመራቸው ተነግሯል።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page