top of page

መጋቢት 20፣2016 - የሰሞኑ የአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ስራ ‘’ቅይጥ የመሬት አጠቃቀምን’’ የሚከተል ነው ተባለ

የሰሞኑ የአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ስራ ‘’ቅይጥ የመሬት አጠቃቀምን’’ የሚከተል ነው ተባለ።


ቅይጥ የመሬት አጠቃቀም፤ ለመኖሪያ፣ የንግድ ስራ እና ለአገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች አንድ ቦታ ላይ እንዲገነቡ የሚያደርግ መሆኑን ሠምተናል።


ይህም ቀደም ሲል የነበረውን የመሬት አጠቃቀም የቀየረ ነው ሲል፤ ከ18 ኪሎ ሜትር የሚበልጠውን የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ያጠናው ድርጅት ነግሮናል።


ቀደም ሲል የሚታወቀው የመሬት አጠቃቀም የመኖሪያ አካባቢ፣ የንግድ ቦታዎች፣ የኢንቨስትመንት ስፍራዎች በሚል የሚከፋፈል እንደነበር ‘’ኮምፓስ ኤፒድ ኮንሰልተንሲ’’ የተሰኘው የዚሁ አማካሪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጎሣዬ በቀለ አስታውሰዋል።


በቅይጥ የመሬት አጠቃቀም፤ አንድን ህንጻ በተለያየ ደረጃ በመከፋፈል ለመኖሪያም ለንግድም ማዋል እንደሚቻል የሚያነሱት ኢንጂነር ጎሣዬ፤ እንዲህ አይነቱ የመሬት አጠቃቀም የአንድ አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።


በመልሶ ልማቱ የመኖሪያ ህንጻዎችም ሆኑ የንግድ ተቋማት ከመንገዶች ገባ እንዲሉ ትኩረት ተሰጥቷል ተብሏል።

ኮምፓስ ኤፒድ ኮንሰልተንሲ* የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት አስመልክቶ ባካሄደው ጥናት ላይ፤ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሞያተኞች እንዳሳተፈ ሠምተናል።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page