የአዲስ አበባ ወንዞች በቆሻሻ የተበከሉ መሆናቸው የከተማ ከርሰ ምድር ውሃ መበከል ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡
በከተማዋ ያሉ 76 ወንዞችና ገባሮች የተበከሉ መሆናቸው የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
የእነዚህ ወንዞች መበከል ደግሞ ከተማዋ ያላት #የከርሰ_ምድር ውሃ ጭምር እንዲበከልና በከተማዋ የመጠጥ ውሃ እጥረት እንዲኖር ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ ይሄንን ያሉት ዛሬ በከንቲባ ፅ/ቤት በቅርቡ በወጣው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት ደንብ ላይ ለመወያየት በተጠራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
የወንዝ ብክለት ደረጃ በሚል ባቀረቡት ፅሁፍ በከተማዋ ባሉ 76 ወንዞችና ገባሮች የተበከሉ መሆናቸውን ተናግረው ይህም ለከተማዋ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት እንዲኖርና የከርሰ ምድር ውሃውም ንጹህ እንዳይሆን አድርጓል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ወንዞች የ #ቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦ ሆነው እያገለገሉ መሆናቸውን አቶ ለሜሳ ጉደታ አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት #የአዲስ_አበባ_የአካባቢ_ጥበቃ_ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ በበኩላቸው የከተማዋ ወንዞች በከፍተኛ ኬሚካል ጭምር የተበከሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ቆሻሻ መጠራቀሚያ እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ እና የኢንዱስትሪ ፍሳሾች ማጠራቀሚያ የከተማዋ ወንዞች ሆነዋል ብለዋል አቶ ዲዳ፡፡
በዚህም ምክንያት በከተማዋ ያሉ #ወንዞች በሽታቸው ምክንያት ሰው በአካባቢያቸው ለማለፍ እስኪቸገር መቆሸሻቸውን አስረድተዋል፡፡
በከተማ ያሉ ወንዞች ለከተማ ግብርና ለመዝናኛ ለዓሣ ማሪቢያና ለተለያዩ አገልግሎቶች መሆን ሲገባቸው የቆሻሻ መጣያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አዲስ አበባን እንደ ስሟ እና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን የሚጠጥን ልማት ያስፈልጋታል ያሉት ስራ አስኪያጁ ያንን ካላደረግን አፍንጫችንን ይዘን ስብሰባ መቀመጥ እና አፍንጫችንን ይዘን መመገባችን የማይቀር ነው ብለዋል፡፡
በከተማ ያሉ ወንዞች የተበከሉ መሆናቸው በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የጤና እክል እያስከተሉ መሆናቸውን ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡
ባለፈው ወንዞችን ከብክለትና ከቆሻሻ ማስወገጃነት ለመከላከል የወጣው ደንብ ከጤና ተቋማት ፣ ከትምህርት ፣ ከነዳጅ ማደያዎች ፣ ከጋራዦች ፣ ከመኪና ማጠቢያዎች የሚወጡ የተለያዩ በካይ ኬሚካኤል ፍሳሽ በወንዝና ከወንዝ ዳርቻዎች ማከማቸት ወይንም መልቀቅ እስከ 400 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሆኖ በደንቡ መደንገጉ ይታወቃል፡፡
ከመኖሪያ ቤት ከመፀዳጃ ቤት ወይንም ማንኛውም ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀ ወይንም መስመሩን አገናኝቶ ወንዙን የበከለ በግለሰብ እስከ 150 ሺህ ብር ፣ ለድርጅት ደግሞ እስከ 300 ሺህ ብር የሚያስቀጣ መሆኑም በደንቡ ላይ ሰፍሯል ይታወቃል፡፡
አዲሱ ደንብ በወንዞች ላይ ለሚታየው ብክለት አንድ መፍትኤ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios