top of page

መጋቢት 2፣2016 - በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶቻቸውን ወደ ሩሲያ እንዲልኩ ከስምምነት መደረሱ ተነገረ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶቻቸውን ወደ ሩሲያ ገበያ እንዲልኩ ከስምምነት መደረሱ ተነገረ።

 

ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶች በሩስያ ሰፊ ገበያ እንዳለ በጥናት ተረጋግጧል ተብሏል።

 

ይህንን በጥናት አረጋግጠናል ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ነግረውናል።

 

ይህንን ገበያ ለመጠቀም የሚስችል ስምምነት ዛሬ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በመከሩበት ወቅት መደረሱንም አክለዋል

 

የሩሲያን ገበያ ከመጠቀም ባሻገር የሀገሪቱ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው እንዲሰሩ ሰፊ የማግባባት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ዘመን ነግረውናል።

 

በድሬደዋ ፣ ሃዋሳና ጅማ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ለመስራት የተስማሙ የሀገሪቱ ባለሃብቶች፤ አሁን ላይ ስራ ለመጀመር  በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ ብለውናል።

 

በነበረው ውይይት ኢንቨስትመንት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ባሻገር፤ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በሩሲያ በኩል ለማመቻቸት ስምምነት መደረሱ ተነግሯል።


 ንጋቱ ረጋሣ 





 


 


 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page