top of page

መጋቢት 2፣2016 ‘’ሴቶችን ለማገዝ ነው የምሰራው እያለ፤ እኛ ሴቶችን ግን ሊሰማን አልቻለም’’ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ቤት ተከራዮች‘’ሴቶችን ለማገዝ ነው የምሰራው እያለ፤ እኛ ሴቶችን ግን ሊሰማን አልቻለም’’ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ቤት ተከራዮች።


የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር አንደ አንድ የገቢ ምንጭ የሚጠቀምባቸው እና የሚከራዩ ቤቶች አሉት።


በቤቶቹ ውስጥ የሚኖሩ እና ለሸገር ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሴቶች፤ በቤቶቹ ውስጥ ከ40 ዓመት በላይ የኖሩም አሉ።


ለቤት ኪራይም ወርሃዊ አንድ ብርም፣ አምስት ብርም እየከፈሉ ኖረዋል።


አሁን ደግሞ ከ150 እስከ 200 ብር እየከፈሉ ይገኛሉ።


ማህበሩ በቅርቡ የቤት ኪራይ ጭማሪ አድርጎ150 ብር እና 200 ብር ይከፍሉ የነበሩ ተከራዮችም 5000 እና 8000 ብር ክፈሉ ተባልን ብለዋል።


‘’ይህ መደረጉ ገቢያችንን፣ ኑሮአችንን ከግምት አላስገባም ብለን ለመናገር ብንጠይቅም ሊያደምጠን የፈቀደ ሰው አጣን’’ ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል።


"ሴቶችን ለማገዝ ነው የምሰራው እያለ እኛ ሴቶችን ግን ሊሰማን አላቻለም "ሲሉ አስረድተውናል።


‘’የኪራይ ተመኑ አይጨመር አላልንም እያልን ያለነው ጭማሪው ከፍተኛ በመሆኑ ልንከፍለው በምንችለው በአቅማችን ይሁንልን ነው’’ ብለዋል።


‘’ወሳኔው ድጋሚ የማይታይ ከሆነም ጎዳና መውጣታችን ነው’’ ብለው ስጋተቸውን አጋርተዋል።


ሸገር ራዲዮ ቅሬታውን ሰምቶ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበርን ለመጠየቅ ሞክሯል።


የማህበሩ ሀላፊዎች ለቅሬታው መልስ እንዲሰጡ ሸገረ ራዲዮ አንድ ሳምንት ጠብቋል።


ሀላፊዎቹ አንዴ ስብሰባ ናቸው፣ሌላ ጊዜ አልገቡም የሚል መልስም አግኝተናል።


በዚህም ምክንያት መልሳቸው አልተካተተም።ንጋቱ ሙሉየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
댓글


bottom of page