መጋቢት 19 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ግዙፋን የመዝናኛ አገልግሎት አቅራቢ ዲ ኤስ ቲቪን ለደንበኞቹ በእጅ ስልክ አቀረበው።
- sheger1021fm
- Mar 28
- 2 min read
ዛሬ በአፍሪካ ግዙፉ የ ቴሌኮም ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቀዳሚው የኢንተርቴይመንት ኩባንያ መልቲ ቾይስ አፍሪካ ሆልዲንግስ የዲኤስ ቲቪ አገልግሎት ስትሪም ጥቅሎችን ይፋ አድርገዋል።
ሁሉቱ ግዙፍ ኩባንያዎች ዛሬ የመዝናኛውን አለም በሐገርኛ አዋዝቶ ለማዘመን የሚያስችል የአጋርነት አገልግሎት አስጀምረዋል።
ስምምነቱ ደንበኞች ዘመናዊ የፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔትና ሞባይል ዳታ ጥቅል አማካኝነት የተለያዩ የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የመዝናኛ ቻናሎችን በጥቅል (package) አመራጭ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡
አገልግሎቱ የተለያዩ ወርሃዊ የሞባይል ዳታ ጥቅል አማራጮችን የያዘ ነው።
የዲኤስቲቪ ጎጆ፣ ቤተሰብ፣ ሜዳ፣ ሜዳ ፕላስ እና ፕሪሚየም ሀገርኛ ጥቅሎችን ጨምሮ የሀገር ውጪ ቻናሎችን እስከ 35 በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸውን ጥቅሎች በቀላሉ በቴሌብር እና በኢትዮ ገበታ *999# ገዝቶ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ለደንበኞቹ የፋይበር መስመር ማንጠፉን ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮም ከመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር የዲኤስቲቪ ቻናሎችን ከብሮድባንድ ኢንተርኔት እና ሞባይል ጥቅል ጋር (Bundle) ለማቅረብ የሚያስችል አገልግሎቱን የ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የመልቲ ቾይዝ ኢትዮዽያ ዋና ዳይሬክተር ገሊላ ገ/ ሚካኤል በይፋ አስጀምረዋል።
ደንበኞች በፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔት አማካኝነት እስከ 26.5 በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸውን ጥቅሎችን በሽያጭ ማዕከሎች በመግዛት በፈለጉት ቦታ ሆነው የመዝናኛ ፕሮግራሞችን መከታተል ይችላሉ ተብሏል።
በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም በ አንድ አመት ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አዲስ አበባን የፋይበር መስመር አነጥፍላታለሁ አለ።
ኩባንያው ለዘመናት ሲያገለግል የነበረውን የ ኮፐር አገልግሎት ወደ ፋይበር እየቀየረ መሆኑን ተናግሯል።
ከ100 አመታት በላይ አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን የደንበኞች የኮፐር ቴሌኮም መስመር ከኮፐር ወደ ፋይበር የሚቀየረው የድምጽና የዳታ ጥራትን ከፍ ለማድረግ እና የደንበኞችን ፍላጎት ከፍ ለማድረግ ነው ተብሏል።
ይህ መሆኑ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና እድገትን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዝ እንዲሁም ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መሆኑን ኩባንያው ተናግሯል።
በዘንድሮ በጀት አመት 100 ሺህ ደንበኞቹን የ ፋይበር መስመር ለማንጠፍ አስቦ በ እቅዱ እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።
ከዚህ ባለፈም የአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች ፕራይቬት ፕሪምየም የ ፋይበር አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
ኩባንያው ፕሪምየም ዋይ ፋይ ለደንበኛ በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስረድቷል።
ይህ በመሆኑም ደንበኛው ከጥገና ጋር በተገናኘ አድካሚውን ስራ ያስቀርለታል ተብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments