መጋቢት 19 2017 - ለሀገር ውስጥ ምርቶች የሚሰጠው አመለካከት መስተካከል ይገባዋል ተባለ።
- sheger1021fm
- Mar 28
- 1 min read
ለሀገር ውስጥ ምርቶች የሚሰጠው አመለካከት መስተካከል ይገባዋል ተባለ።
የሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲበረታቱም በቅድሚያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሻሻል እንደሚገባም ተነግሯል።
በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ላይ አለ የሚባለው የጥራት ችግርም አንፃራዊ ነው ተብሏል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ፅ/ቤት የአቅም ግንባታ እና የምርምር ተቋም አስተባባሪ አቶ ዬናስ መኩሪያ በሀገር ውስጥ ተሰማርተው የሚያመርቱ አምራቾች በህብረተሰቡም ሆነ በመንግሥት ደረጃ የማይበረታቱ ከሆነ በምርት ጥራትም፣ ብዛትም ተወዳዳሪ መሆን አይችሉም ብለዋል።
አያይዘውም መንግስት የሚገለገልባቸው ቁሶችም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments