በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 3 ዓመታት የ5 የሰብል አይነቶችን ምርጥ ዘር ለማብዛት እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
ይህም የሆነው በሀገሪቱ የሚታየው የዘር እጥረት ስርጭትን ለመፍታት ነው የተባለ ሲሆን በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል ምርጥ ዘር ለመሰብሰብ ውጥን ተይዟል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) እንዳሉት ‘’ትኩረት የተሰጣቸው የሰብል አይነቶች ስንዴ በቆሎ ገብስ ጤፍ እና ማሽላ’’ ናቸው፡፡
እነዚህ ሰብሎች የሀገሪቱን 87 ከመቶ የምግብ ፍላጎት ይሸፍናሉ የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ እየሰራች ላለችው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምርጥ ዘር ፍላጎቱ ሟሟላት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ተብሏል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከነዚህ ውጪ ያሉ የሰብል አይነቶች የዘር አቅርቦትና ብዜት ስራዎች ጎን ለጎን እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
コメント