መጋቢት 18 2017 - ‘’ውል ላልያዙ እና ውላቸው ለተቋረጠ ሰራተኞች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከፍሏል’’ የተባለው ተቋም
- sheger1021fm
- Mar 27
- 1 min read
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያላግባብ ወጪ ያደረገውን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር እና ሌሎች በኦዲት ምርመራ የተገኙ የአሰራር ግድፈቶችን አስተካክሎ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለፓርላማው እንዲያሳውቅ ታዘዘ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በፕሮጀክትና ውል ላልያዙ እንዲሁም ውላቸው ለተቋረጡ #ሰራተኞች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር መክፈሉም ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
በኦዲት ምርመራ ከተረጋገጡት መካከል ጥቂቶቹ
- በድምሩ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ወጭ ተደርጓል፡፡
- በውሉ መሰረት 493 ሺህ ብር መከፈል ላለበት አገልግሎት 4.4 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል፡፡
- ውል ለሌላቸው እና ውላቸው ለተቋረጡ ሰራተኞች በድምሩ ወደ 2 ሚሊዮን ብር የተጠጋ ብር ተከፍሏል፡፡
- የሚከወኑ ፕሮጀክቶች የቅድሚያ አዋጭነት ጥናት አይካሄድም፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments