top of page

መጋቢት 18 2017 - ተጭበርብረው ከሀገር የወጡና በማይናማር ስካም ሴንተር ውስጥ ከቆዩ መካከል 14 ኢትዮጵዊያን ዛሬ አዲስ አበባ መድረሳቸው ተሰምቷል

  • sheger1021fm
  • Mar 27
  • 1 min read

በተለያዩ የድንበር አስተላላፊዎች እና ህገ ወጥ የውጪ ሀገር የስራ ስምሪት አከናዋኞች አማካይነት ተጭበርብረው ከሀገር የወጡ እና በማይናማር ስካም ሴንተር ውስጥ ከቆዩ መካከል 14 ኢትዮጵዊያን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መድረሳቸው ተሰምቷል፡፡


በታይላንድ እና ማይናማር የድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች አጭበርባሪዎች ባቋቋሟቸው ለስካሚንግ ሴንተሮች ውስጥ በአይነ መረብ የኦን ላይን የገንዘብ ማጭበርበር ስራ ላይ በግዳጅ የተሰማሩ የተለያዩ ሀገር ዜጎች መኖራቸው በመታወቁና ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ በመጀመሩ በህገ ወጥ ቡድኖች ስር ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል በተለያዩ ጊዜያት የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን አምልጠው ታይላንድ መግባታቸው ተነግሯል፡፡


ከህገወጥ ቡድኖቹ ነፃ የሆነና ታይላንድ በመገባት ወደ ሀገር ለመምጣት ድጋፍ ይጠባበቁ ከነበሩት መካከል የ14ቱ ወጪ በድርጅት ተሸፍኖ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡና አጋዥ በመፈለግ የተባበረው ሀገር በቀል ድርጅት የስራ ሀላፊ ዳንኤል መለሰ ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page