top of page

መጋቢት 18 2017 - ''በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነው''

  • sheger1021fm
  • Mar 27
  • 1 min read

በደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ ስደት ሰለባ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እስከ ሞት የደረሰ የተለያየ ችግር እንደሚጋጥማቸው ተደጋግሞ ይነገራል፡፡


በተለይ ለዚህ ችግር ተጋላጭ ናቸው የተባሉትን ሴቶችን በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ በማገዝ ህገወጥ ስደትን ከስሩ ለማስቀረት እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


#የሴቶችና_ማህበራዊ_ጉዳይ ሚኒስትር እርጎጌ ተስፋዬ በህገወጥ መንገድ ወይንም መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሚፈልሱት አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን አንስተው በተለይ ሴቶች የዚሁ ሰለባ እንዳይሆኑ በሚል በገጠር አካባቢ ያሉትን በግብርናው ዘርፍ ተሰማርተው የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።


ለህገወጥ ወይንም መደበኛ ላልሆነ ፍልሰት ብዙዎቹ የሚጋለጡት ከድህነት ባለፈ በሀገሪቱ ባለው #ግጭቶች ሳቢያ እንደሆነም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።


በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩት ላይ ጥቆማ እየደረሰን በመሆኑ በአዘዋዋሪዎቹ ላይ እርምጃ አየተወሰደባቸው ነውም ብለዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

Commenti


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page