መጋቢት 18 2017 - ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ለመሾም የተጠራውን የጥቆማ ጥሪ በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ሕወሓት “ተቀባይነት የለውም” አለ
- sheger1021fm
- Mar 27
- 1 min read
ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ለመሾም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት የተጠራውን የጥቆማ ጥሪ በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ሕወሓት “ተቀባይነት የለውም” አለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት ለመሾም ሕዝቡ እንዲሳተፍበት ጥሪ መቅረቡን ሕወሓት የተቃወመው ትናንት ባወጠው መግለጫ ነው፡፡
በመግለጫው የጊዜዊ አስተዳደሩን ለመሾም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን መሆኑን የሚጠቁመውን አንቀፅ አግባብነት የሌላቸው ሕጎች መሆናቸውን ጠቅሶ ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሃት ስምምነት የሚቋቋመው ነው ብሏል፡፡
ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንጂ የኢትዮጵያ የተናጠል ውሳኔ ውጤት አይደለም የሚለው ሕወሃት አሉታዊ ድርጊት በመፈፀም የፌዴራል መንግስቱን ከሷል፡፡
በስምምነቱ የሌሉ ጥሰቶችን በመፈፀም፣ አሉታዊ ፕሮፓጋንዳዎች በማሰራጨት፣ የትግራይን ታጣቂዎች ስም በማጥፋት፣ እስካሁን የተመረጠ መንግስት እንዳይኖር ፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አፈፃፀም በተሳሳተ አቅጣጫ በማስያዝና ተፃራሪ ተግባራት በመፈፀም ፣ወደ ክልሉ የሚደርሱ ወሳኝ ሸቀጦችን በመገደብ ፣የፌዴራል መንግስቱን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ለጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ እንዲሆን የተስማሙበት ቀርቶ ወደምርጫ ጥቆማ መግባቱን አልቀበልም ብሏል፡፡
ነገር ግን ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ፕሬዝዳንት እንዲሆን ስምምነት፣ የተፈፀመው መቼ እንደሆነ በመግለጫው ላይ አልጠቀሰም፡፡
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ለመሾም ሕዝቡ ተሳትፎ እንዲኖረው ጥቆማ እንዲያድርግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራ ከጀመረ በኋላ፣ በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳና፣ በዶ/ር ደብረፂዮን የሚመሩት የህወሃት ቡድኖች አንዱ ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ በጭቅጭቅ መክረማቸው ይታወሳል፡፡
እሸቴ አሰፋ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
コメント