top of page

መጋቢት 18፣2016 - የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት በሚያስገባቸው የግብርና ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥሩን እያጠበቀ ነው ተባለ።

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት በሚያስገባቸው የግብርና ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥሩን እያጠበቀ ነው ተባለ።


የህብረቱን የጥራት መስፈርት ለማሟላት ኢትዮጵያውያን ላኪ ነጋዴዎች ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።


ኢትዮጵያውን ነጋዴዎች ቡና እና ሰሊጥን ጨምሮ በርከት ያሉ የግብርና ምርቶችን ወደ አውሮፓ ህብረት አባል አገራት ይልካሉ።


በተለይ ህብረቱ ከጦር መሳሪያ በስተቀር ሁሉም ምርቶች ወደ ገበያው እንዲገቡ የሰጠው ዕድል ኢትዮጵያውን ላኪዎችን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ አድርጓል ተብሏል፡፡



ከዚሁ ጎን ጎን ህብረቱ በሚቀበላቸው ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥሩን እያጠበቀ እንደሚገኝ ተሠምቷል።


ኢትዮጵያውን ላኪዎችም ይህንኑ አውቀው መስራት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፀሃፊ አቶ ስዩም ጫኔ ተናግረዋል።


ህብረቱ ሊተገብረው ያሰበው የጥራት ህግ የምርቱን መነሻ ፤ የማጓጓዝ ሂደት እና የማከማቻ ስርአት የሚፈትሽ እንደሆነ አቶ ስዩም ተናግረዋል ።


ህብረቱ እነዚህ አስገዳጅ የጥራት መስፈርቶች በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ስራ ላይ ያውላቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የሰማነው።

Comments


bottom of page