top of page

መጋቢት 17 2017 - ኢትዮዽያ የእንግሊዙን ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ አዲስ አበባ አመጣች

  • sheger1021fm
  • Mar 26
  • 1 min read

ዋና መስሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮጵያን 80ኛ መዳረሻው በማድረግ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል።


ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ያደረገው በመኪና ኪራይ ዘርፍ ላለፉት 10 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ኤክሰለንት የመኪና ኪራይ ድርጅት ነው፡፡


ስራውን በአዲስ አበባ እውን ለማድረግ ሁለት ዓመት የፈጀ ድርድር ሲደረግ መቆየቱን ሰምተናል፡፡


በተለይ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ለስብሰባ ለመሳሰሉት ጉዳዮች አዲስ አበባን የሚረግጡ ተጓዦች በቆይታቸው የመኪና ኪራይ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ገና ከመምጣታቸው አስቀድሞ የመኪና አይነቱንም ክፍያውንም መፈፀም እንደሚችሉ ተናግሯል።


ይህ በመሆኑም የሀገርን ገፅታ ከፍ ያደርጋል የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም ለመፍጠር እድል ነው ተብሏል።


የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ከየትኛውም አለም በግሪንሞሽን ኢትዮጵያ ድረ ገፅ እና መተግበሪያዎች በመግባት የመኪና ኪራይ ውል ማሰር እና በተቀመጠው አማራጮችም ክፍያ መፈፀም ይችላሉ ተብሏል፡፡


ዋና አገልግሎቱ ለቢዝነስ፣ ለስብሰባ፣ ለጉብኝት ለመሳሰሉ ከውጭ ሀገር ለሚመጡ ሰዎቸ ቢሆንም ሀገር ውስጥ ያሉ ደንበኞቹን እንደሚያስተናግድ ሰምተናል፡፡

በኤክሰለንት የመኪና ኪራይ በኩል ግዙፉ ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ በተለይ ለቱሪዝሙ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታ እንደገና አበበ ተናግረዋል፡፡


የግሪን ሞሽን ኢትዮዽያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ በንግግራቸው ግሪን ሞሽን በኢትዮዽያ ስራ መጀመሩ ለሀገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከማምጣትም ባለፈ በጎ ገፅታዋን ለአለም ለማሳየት እድሉን ይከፍትላታል ብለዋል።


የግሪን ሞሽን ኢትዮዽያ አለም በእጅጉ የሚያስፈልጋትን ለአየር ንብረት ለውጥ በጎ አስተዋፅኦ በሚያደርጉ አሰራሮች መቃኘቱ ለኢትዮዽያ ያግዛል ብለዋል።


አቶ ብዙአየሁ ይህ አለም አቀፍ ኩባንያ ወደ ሀገራችን አምጥተን አገልግሎት በማስጀመራችን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያስገኝልናል፤ ከነዚህም ውስጥ የእውቀት ሽግግር፣ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት፣ የስራ እድል፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የእንግዶች እርካታ ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page