መጋቢት 15 2017 - የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር 4 ቀን ሙሉ የኤልክተሪክ ሃይል ስለተቋረጠበት ከ24 በላይ የባቡር ጭነቶች ሳይጓጓዙ መቅረታቸውን ተናገረ
- sheger1021fm
- Mar 24
- 1 min read
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር 4 ቀን ሙሉ የኤልክተሪክ ሃይል ስለተቋረጠበት ከ24 በላይ የባቡር ጭነቶች ሳይጓጓዙ መቅረታቸውን ተናገረ፡፡
በዚህም ምክንያት ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች መርከብ እንዳመለጠ ሰምተናል።
እነዚህ ጭነቶች ገቢና ወጭ እቃዎች ሲሆኑ ብረት፣ ዘይት፣ ማዳበሪያና ሌሎችም ሸቀጦች ይገኙበታል ተብሏል።
በ4 ቀን ውስጥም 8 #የባቡር_ትራንስፖርት መሰረዙን ሰምተናል።
የዚህ ችግርም የኤሌክትሪክ ሀይል የአገልግሎት መቋረጥ ነው ተብሏል።
በጭነት ገቢና ወጭ እቃዎች መካከል ሊበላሽ የሚችሉ ጭነቶች ቢኖሩም፣ የባቡር የትራንስፖርት አገልግሎትን በሌላ የሀይል አማራጭ በመጠቀም ጅቡቲ ወደብ ማድረስ መቻሉን ሰምተናል።
የይህን መስተጓጎል ለማካካስ በመጪዎቹ ቀናት ለደንበኞች፣ የጅምላ ጭነት እና የኮንቴይነር ጭነት አገልግሎት እያመቻቸ መሆኑን የኢትዪ ጅቡቲ ምድር ባቡር ተናግሯል።
እያንዳንዱን ፉርጎ እና ኮንቴነር በተናጠል ከመቁጠር ይልቅ የባቡር ጉዞ ቁጥሩን በመጠቀም በጅቡቲ ጉምሩክ ያለውን የሰነድ አሰጣጥ ሂደት ቀላል እያደረገ መሆኑን አገልግሎት ሰጭው ተናግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ተህቦ ንጉሴ
Comments