መጋቢት 15 2017 - ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ብትሆን ምን ትጠቀማለች?
- sheger1021fm
- Mar 24
- 1 min read
ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት ( #WTO ) አባል ለመሆን እየተደራደረች ነው፡፡
ድርድሩ የተሳካ መሆኑንንም የመንግስት ሀላፊዎች እየተናገሩ ነው፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ብትሆን ምን ትጠቀማለች? ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) በጉዳይው ላይ ጥናታዊ ጸሁፍ ሰርተዋል፡፡
እርሳቸው ሀገሪቱ ድርድሩ ተሳክቶላት የድርጅቱ አባል መሆን ከቻለች የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና የወጪ ምርትን ለማሳደግ እንደሚረዳት አስረድተዋል፡፡
ሸማቹ ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ይረዳዋል ሲሉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments