top of page

መጋቢት 14፣2016 - ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቼክ ክፍያዎችን በባንኩ እንዲመነዘሩ ለደንበኞቹ ጥሪ አቀረበ

ባንኩ ይህን የተናገረው ደንበኞች ከቼክ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ስጋት እንዳይገባቸው በማሰብ ነው ብሏል።


ንብ ባንክ በብሔራዊ ባንክ አመቻችነትና ታዛቢነት ባደረገው ምርጫ የተመረጡት የቦርድ አባላት፤ ባንኩን እንዲያስተዳድሩ ከተፈቀደለት በኃላ ዛሬ 20ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎል።


ለባንኩ አዲስ የተቋቋመለት ቦርድ ባንኩ የነበረበትን ችግሮችና እንቅፋቶች ለይቶ ወደ ስራ መግባቱን ሰምተናል።

ለዚህም ባንኩ ዳግም እንዲነቃቃና በቢዝነስ ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ያግዛሉ የተባሉ እርምጃዎች ተወስደዋል ተብሏል።


አዲሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከቀድሞ ቦርድ ርክክብ ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ፤ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኩል ያሉትን ችግሮች ለማወቅና መፍትሔ ለማበጀት በተከታታይ በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጡንም ሰምተናል።


የደንበኞችን አመኔታ በአጭር ጊዜ እንዴት ማስመለስ ይቻላል የሚል የመፍትሄ ሰነድ ከተዘጋጀ ከኋላ ወደ ስራ መግባቱን ባንኩ ተናግሯል።


በባንክ ገበያ ውስጥ የተሻለ ስራ ለማከናወን በመላው ሀገሪቱ በዳግም የማርኬቲንግ ስራ መጠመዱን ንብ ባንክ አስረድቷል።

ንብ ባንክ ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ወቅታዊ የሆነ የገንዘብ እክልና አስተዳደር ችግር እንዳጋጠመው መነገሩ ይታወሳል።


በብሔራዊ ባንክ አመቻችነት የተመረጠው አዲሱ ቦርድ የተጣለበትን አደራ ተገንዝቦ ባንኩ ከነበረበት ሁኔታ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚተጋ ቃል ገብቷል ተብሏል።


ንብ ባንክ ባጋጠመው ችግሮች ምክንያት መጉላላት እና ቅሬታ ለተፈጠረባቸው ባለ አክስዮኖችና ደንበኞች ይቅርታ ጠይቋል።


ደንበኞች ንብ ባንክ የቼክ ክፍያዎች አይፈፅምም የሚል ስጋት በፍፁም እንዳይኖራቸው ሲል ተናግሯል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የቼክ ክፍያዎችን በባንኩ እንድታደርጉ ሲል ጠይቋል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page