top of page

መጋቢት 14፣2016 - ሰሞኑን ህይወታቸው አልፎ የተገኙት የዶ/ር በሀይሉ አሟሟት ከከፍታ ቦታ በመውደቅ ነው ሲል ፖሊስ ተናገረ

ሰሞኑን ህይወታቸው አልፎ የተገኙት የሰርጀሪ ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር በሀይሉ አሟሟትን ከከፍታ ቦታ በመውደቅ ነው ሲል ፖሊስ ተናገረ፡፡


የአዲስ አባበ ፖሊሰ ኮሚሽን ይህን ያልኩት የሆስፒታል ምርመራን ውጤትን ጠቅሶ ነው፡፡


በዚህም ዶክተር በሃይሉ ሀይሉ ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ እንዳረጋገጠ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስረድቷል፡፡


የሰርጀሪ ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ ም በዕለተ እሁድ ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው እንዳልተመለሱ እና ህይታቸው አልፎ መገኘቱን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ ቆይቷል።


ፖሊስ ባደረኩት ማጣራት የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ ማሞ ድልድይ ስር ወድቆ መገኘቱን ተናግሯል፡፡


የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓል ተብሏል፡፡



የአስክሬን ምርመራ ውጤት ሃኪሙ ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ አስረድቷል ተብሏል፡፡


ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል፡፡


ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መቀጠሉንም ተናግሯል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page