መጋቢት 12 2017 - ደንቡ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆነው ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ሲወጣለት መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተናገረ
- sheger1021fm
- Mar 21
- 1 min read
አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽት 4:00 እንዲሰሩ ለማድረግ የወጣው ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆነው ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ሲወጣለት መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተናገረ፡፡
በከተማዋ የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች ሱቆች እና ሌላም የንግድ አገልግሎት ሰጭዎች እስከ ምሽት በራቸውን እንዳይዘጉ ወይም በራቸው ዝግ ከሆነ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት በራቸው ላይ እንዲያኖሩ የሚያስገድደው ደንብ ከመጋቢት 10 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገብቷል ተብሎ ነበር፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የደንቡን አተገባበር አስመልክቶ ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር በዛሬው ዕለት ባደረገው ውይይት ከነጋዴው ወገን በርካታ ቅሬታዎች ተነስተዋል።
አምሽተን ስንወጣ የስራና የመኖሪያ ቦታችን የተራራቀ በመሆኑ የደህንነት ስጋቶች አሉብን፤ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሱቃችንን ብንዘጋ፤ በድንገት መብራት ቢጠፋ በደምቡ ላይ በር እንዳይዘጋ ማብራት እንዳይጠፋ የሚል ስለተቀመጠ ብቻ መቀጣት የለብንም የሚሉና መሰል ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።
ውይይቱን የመሩት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በሰጡት ምላሽ ስጋታችሁን እንረዳለን የወጣው ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆነው ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ሲወጣለት ነው ብለዋል።
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments