top of page

መጋቢት 12 2017 - የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Mar 21
  • 1 min read

በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን ለማከም ከእልፈት በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡


ነገር ግን የለጋሾች ብዛት ቢጨምርም የህክምና ግብዓትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ማነስ ብዙ እንዳይሰራ ማድረጉ ተነግሯል።


ከዚህ ቀደም የነበሩ ስራዎች በሚፈለገው መጠን አልነበሩም ተብሏል፤ አሁን ግን በተለይ ተቋሙ ራሱን ችሎ የኢትዮጵያ ደምና ህብረዋስ ባንክ በሚል ዳግም ከተቋቋመ በኋላ የተሻሻሉ ለውጦች እንደታዩ ተነግሯል፡፡


አቶ አለማየሁ ታረቀኝ የኢትዮጵያ ደምና ህዋስ ባንክ አገልግሎት የዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ እንደነገሩን የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተደረገ ምክክር በኋላ የአይን ብሌናቸው ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ይላሉ፡፡


#የዓይን_ብሌን በልገሳ ከተገኘ በኋላ ህክምናውን ለማድርግ የግብዓትና በዘርፉ ያሉ ቀዶ ህክምና የሚያከናውኑ ባለሙያዎች ጥቂት መሆን ብዙ እንዳይሰራ አድርጎታል ሲሉ አቶ አለማየሁ ነግረውናል፡፡

ህክምና የሚሰጡ ሀኪሞች ቁጥራቸው በጣም ትንሽ ነው ያሉን አቶ አለማየሁ አሁንም ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ከ12 የዘለላ አይደለም ብለዋል፡፡


ከአዲስ አበባ ውጪ የዓይን ባንክ ለመክፈትና በክልሎችም አገልግሎቱን ለመስጠት በዚህ አመት የተጀመሩ ስራዎች አሉ ተብሏል፡፡


ይህም በአንድ ቦታ በማዕከል ብቻ የነበረውን አገልግሎት በማስፋት ብዙዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡


የህክምና ግብዓቶችን ለማሟላትና ባለሙያዎችንም የማሰልጠን ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል፡፡


ከእልፈት በኋላ የዓይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ ቃል ለማስገባት የታቀደው ሶስት መቶ ሲሆን ከዕቅዱ በላይ በስድስት ወራቱ 5 መቶ ሰዎች ቃል መግባታቸው ተነግሯል፡፡


ባለፈው ዓመት ብቻ በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን ላጡ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ በማድረግ ብርሃናቸው እንደተመለሰላቸው ሰምተናል፡፡


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page