መጋቢት 12 2017 - ከተቀጣሪው ደመወዝ ላይ መንግስት ለአደጋ ጊዜ ፈንድ በሚል በየወሩ ገንዘብ መቁረጥ ሊጀምር ነው
- sheger1021fm
- Mar 21
- 1 min read
ከተቀጣሪው #ደመወዝ ላይ መንግስት ለአደጋ ጊዜ ፈንድ በሚል በየወሩ ገንዘብ መቁረጥ ሊጀምር ነው፡፡
የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ ለሚደርሱ የተለያዩ አደጋዎች በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ደንግጓል፡፡
ለዚህም ደመወዝተኞች በየወሩ ከደመወዛቸው እንዲያዋጡ እንዲሁም የንግድ ፈቃድ ሲያወጡም ሆነ ሲያድሱ በቁርጥ ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚስገድድ ነው፡፡
ደመወዝተኛው እስካሁን እስከ 35 በመቶ የገቢ ግብር፣ 7 በመቶ የጡረታ በድምሩ 42 በመቶ ድረስ በየወሩ ሲቆረጥበት ቆይቷል፡፡
ይቋቋማል ለተባለው የአደጋ ፈንድ ምን ያህል በመቶ እንዲቆረጥ ግን እስካሁን አልታወቀም፡፡
ተቋማትም መዋጮ እንዲያደርጉ የሚገደዱ ይሆናል የተባለ ሲሆን ምን ያህል በመቶ ያዋጣሉ ለሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዝርዝር ደንብ ይወጣል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios