top of page

መጋቢት 12 2017 - ኢትዮጵያ የጨረር ህክምና የኒውክለር የህክምና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት እንዳለባት ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • Mar 21
  • 1 min read

የካንሰር ህመም ከጤና ችግርነቱ ባለፈ ለህክምና በሚጠይቀው ወጪ እና ረዘም ያለ ጊዜ ምክንያት የዜጎችን ኪስ እየፈተነ የሀገርንም ኢኮኖሚ ይጎዳል፡፡


ኢትዮጵያ ለ #ካንሰር_ህክምና የሚውለውን የጨረር ህክምና ለማድረግ የሚያግዘውን ግብዓት በውጭ ምንዛሪ ገዝታ ነው የምትጠቀመው፤ ይህም ህክምናው ብዙ ገንዘብ እንዲጠይቅ አድርጎታል ተብሏል፡፡


ለዚህም መፍትሄ የተባለው ሀገሪቱ የጨረር ህክምና እንዲሁም ሌሎች ለምርመራ የሚሆኑ ሥራዎችን ለመስራት የኒውክለር የህክምና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት እንዳለባት ተነግሯል።


የኒውክለር የህክምና ቴክኖሎጂ ካንሰር በሰውነት ውስጥ ሳይሰራጭ ገና ከጅምሩ ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎችን እንዲሁም ከተከሰተ በኋላም ለህክምና ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን የሚናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ኒውክለር ፋርማሲስት እና መምህር የሆኑት ዶክተር ዮሃንስ ጆርጌላጌቦ ናቸው፡፡


በአሁኑ ጊዜ አለምን በከፍተኛ ደረጃ እያስፈራ ያለው ካንሰር ህክምናን ገና በሰውነት ውስጥ ሳይስፋፋና ሳይሰራጭ ለማከም አንደኛው መላ የኒኩለር ቴክኖሎጂ ነው ብለዋል፡፡

የካንሰር ህሙማንም እየተጎዱ በመሆኑ ወደፊት ቴክኖሎጂው በሚስፋፋበት ጊዜ ስራውን እንደሚያሻሽለው ተናግረዋል፡፡


#የኒውክለር_ህክምና ቴክኖሎጂን ሌሎች ሀገራት በስፋት እንደሚጠቀሙበት የሚናገሩት ዶክተር ዮሐንስ በኢትዮጵያ ስራው ቢጀመር ለካንሰር ህክምና የሚወጣውን ውጪ የሚቀንስና አገልግሎቱም ለብዙዎች እንዲዳረስ ያግዛል ይላሉ፡፡


ለካንሰር ህክምና የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እያካሄደ ባለው የካንሰር ህክምና ማዕከል ግንባታው ቴክኖሎጂውን ወደ ስራ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ዶክተር እጅጉ ከበደ የሜዲካል ፊዚስት ስፔሻሊስት ናቸው እርሳቸው እንደሚናገሩት የኒውክለር የህክምና ቴክኖሎጂ ለካንሰር ህክምናና ምርመራ ስራ ላይ ቢውል በብዙ የሚጠቀምነው፡፡


የኒውክለር የህክምና ቴክኖሎጂ በሌሎች የምርመራ መሳሪያዎች የማይታዩና በሰውነቱ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ የካንሰር ቅንጣቶችን በመለየት በጊዜ ለማወቅና ለማከም የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በተለያየ ዓይነት ካንሰር የሚያዙ ሲሆን ከ44 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፤ የጡት እና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ዓይነቶች ደግሞ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://0fj.cc/1WB1p9ZDH54


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page