የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደ ተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳሰበ።
ባለፈው ሳምት አርብ እለት ሌሊት ያገጠመው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱና ያልተገባ የገንዘብ እንቅስቃሴ ካከናወኑ ግለሰቦች መካከል ብዙዎች የተደረገላቸውን ጥሪ አክብረው የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች እየቀረቡ እየመለሱ ነው ሲል ባንኩ ተናግሯል፡፡
እስካሁን ቀርበው ገንዘቡን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦችም እስከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ ተመላሽ እንዲያደርጉ የመጨረሻ ነው ያለውን ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና በተከታታይ የተለያዩ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡
፡
ከቅዳሜ ብኋላ ደረጃ በደረጃ ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ሥም ዝርዝር በየቅርንጫፎች እና እንደሁኔታው ግለሰቦቹ ሊታወቁ በሚችሉበት ኣካባቢ ይፋ እንደሚያደርግ ባንኩ አሳስቧል፡፡
በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ፎቶግራፋቸውን እና ዝርዝር ማንነታቸውን የሚገልፁ መረጃዎች ባንኩ በመረጠው የብዙሀን መገናኛ መንገድ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስጠንቅቋል፡፡
ከዚሁ በላይ ከተጠቀሱት እርምጃዎች ጎን ለጎንም እስከ ቅዳሜ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦችን ከፍትህ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን የወንጀል፣የፍትሐ ብሔርና አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንደሚያስደርግ ባንኩ አሳስቧል።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ያንቀሳቀሱ ግለሰቦች የማይመልሱ ከሆነ በህግ እንደሚጠየቁ መናገሩ ይታወሳል፡፡
ባንኩ አርብ ሌሊት ከ 490 ሺህ በላይ የገንዘብ ዝውውሮች እንደተፈጸሙ ተናግሮ ነበር፡፡
አብዛኛውን የገንዘብ ዝውውር የፈጸሙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነቸው የተባለ ሲሆን እስከ 186 ጊዜ ድረስ የገንዘብ ዝዉዉር የፈጸመ ተማሪ አለ ሲሉ ባንኩ ፕረዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários