top of page

መጋቢት 12፣2016 - ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሀገሪቱን ታላቁን ኒሻን ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ማበርከታቸው ተሰማ

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሀገሪቱን ታላቁን ኒሻን ለጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ማበርከታቸው ተሰማ።


የኒሸን መስጠት ስነ-ስርዓቱ የተካሄደው በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ቤተ-መንግስት ነው ተብሏል፡፡


ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የደቡብ ሱዳን ታላቁን ኒሻን የተበረከተላቸው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ነፃነትና ሉአላዊነት መከበር ለከፈሉት ታላቅ የደም መስዋዕትነትና ድጋፍ ክብር ይገባቸዋል በማለት ነው ተብሏል፡፡


ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ኢትዮጵያ በቸገረን ጊዜ ሁሉ መጠጊያችን መጠለያችን ከመሆኗም በላይ ለዚህ ሀገራዊ ነፃነታችን ክብር የሆኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ልጆቿን ህይወት ጭምር በመክፈል እንደሀገር እንድንቆም ያደረጉ ወለታቸውንም መቼም ከፍለን የማንጨርሰው ባለውለታችን ናቸው ማለታቸው ተሰምቷል።


ዛሬም ድረስ የደቡብ ሱዳንን ሠራዊት አቅም በመገንባት የውስጥ ችግር ሲያጋጥመን ሮጠው በመምጣት ችግራችንን የሚጋሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው ሲሉም ተናግረዋል ተብሏል።


በስነ- ስርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፣ የሀገሪቱ የደህንነት ከፍተኛ ሃላፊዎች ፣ ጄኔራል መኮንኖች መገኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page