መጋቢት 11 2017 - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል ባለው ጊዜአዊ አስተዳደር ውስጥ በግለሰብ ደረጃ የስልጣን ልውውጥ ሊኖር እንደሚችል ተናገሩ
- sheger1021fm
- Mar 20
- 1 min read
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል ባለው ጊዜአዊ አስተዳደር ውስጥ በግለሰብ ደረጃ የስልጣን ልውውጥ ሊኖር እንደሚችል ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግለሰቦች ደረጃ በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ የስልጣን ለውጥ ሊኖር እንደሚችል በዛሬው የፓርላማ ቆይታቸው ተናግረዋል፡፡
በጊዜአዊ አስተዳደሩ ላለፉት 2 ዓመታት ለሰራው ስራ አድናቆት የቸሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጊዜአዊ አስተዳደሩ የሁለት ዓመት የስልጣን ቆይታ አሁን አብቅቷል ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት #የህግ_ማሻሻያ የሚፈልግ ጉዳይ አለ፤ ተጨማሪ ጊዜ ስለሚፈልግ መሻሻል አለበት ህጉ ሲሻሻል ደግሞ የነበረው አፈፃፀም መገምገም አለበት፡፡

ተገምግሞም መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የፕሪቶሪያው ስምምነት ባከበረ መንገድ ጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ስራውን እየሰራ ህዝቡን ለምርጫ ለማዘጋጀት መስራት አለበት ብለዋል፡፡
ይህ ለማድረግ ከክልሉ ጊዜአዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና ከምክትሎቻቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህውሃትን ጨምሮ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋርም ውይይት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ንግግር መሰረት ህግ አሻሽለን ለሚቀጥለው አንድ ዓመት ጊዜአዊ አስተዳደሩ ይቀጥላል የሚል እምነት አለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜአዊ አስተዳደሩ ሲቀጥል ደግሞ በግለሰቦች ደረጃ የስልጣን ለውጥ ሊኖር ይችላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments