መጋቢት 11 2017 - የህዳሴ ግድብ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
- sheger1021fm
- Mar 20
- 1 min read
የህዳሴ ግድብ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ሚንስትሩ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ውቅት እንዳሉት ህዳሴን ከ6 ወር በኋላ እንመርቃለን ብለዋል፡፡
መንግስት ከ #ህዳሴ_ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ መንግስት ጋር በተለይም ከደህንነት መስሪያቤት ጋር ህዳሴን በተመለከተ ውይይት አድርገናል የተለያዩ ሃሳቦችም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቅርበናል ብለዋል፡፡
መንግስት በህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል::
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments