top of page

መጋቢት 11 2017 - በ8 ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፈጠሩን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

  • sheger1021fm
  • Mar 20, 2025
  • 1 min read

ባለፉት 8 ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፈጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


ከመካከላቸው ከ300 ሺህ በላይ በውጭ ሃገር የተቀጠሩ እና በኢትዮጵያ ሆነው ለውጭ ኩባንያዎች የሚሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡


የስራ እድል ተገኝቶላቸዋል ከተባሉት መካከል ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በስራ ስምሪት ባደረገችው ስምምነት ከ300 ሺህ ያህሉ ወደ ውጭ ለስራ የሄዱ ናቸው ተብሏል፡፡


45 ሺህ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በኢትዮጵያ ሆነው በበይነ መረብ ወይም በኢንተርኔት አማካይነት ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ስራ እየሰሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከአባላት ለቀርቡ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል፡፡


በሚከወኑ የኮሪደር ልማቶች ጭምር 2.8 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በሃገር ቤት የስራ እድል እንዳገኙ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፈጠረው የስራ እድል ቀላል የሚባል ባይሆንም ሰፊ ጥረት የሚያስፈልገው ጉዳይ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page