መጋቢት 11 2017 - በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
- sheger1021fm
- Mar 20
- 1 min read
በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ባለፉት ዓመታት በተደረገው ጥናት መሰረት #የማዳበሪያ_ፋብሪካ ግንባታው ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
"አሁን የህዳሴ ጉዳይ እንደምታውቁት ስለሆነ የህዳሴ ፊታችንን ወደ ማዳበሪያ እናዞራለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
‘’በጣም በርትተን ከሰራን ቢያንስ ከሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ጊዜ ይፈልጋል’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም "ሁለተኛ ህዳሴ የሚሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካው ነው" ብለዋል፡፡

‘’ግንባታውን ከተቻለ ከግሉ ሴክተር ጋር በመተባበር ውይም በግል ኢንቨስትመንት ካልሆነም በመንግስት የግድ የማዳበሪያ ፋብሪካ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊመልስ በሚችል መልኩ መገንባት ይኖርበታል ምናልባትም የሚቀጥለው ዓመት ሁነኛ ተግባሩ ይጀምራል’’ ብለዋል፡፡
መንግስት ለአንድ ኩንታል ማዳበሪ 3,700 ብር ድጎማ በማድረግ ለአርሶ አደሩ እያቀረበ መሆኑንን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም መንግስት 84 ቢሊዮን ብር መደጎሙን አስረድተዋል፡፡
በዚህ ዓመት 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በየቀኑም 150,000 ኩንታል ማደበሪያ ከወደብ እየተጓጓዘ መሆኑንን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም መንግስት በ #ወታደር እያጀበ ወደ የወረዳዎች ማዳበሪያ ያጓጉዛል ብለዋል፡፡
ለአብነትም ባለፈው አመት በአማራ ክልል 7,000 የጭነት መኪና ማዳበሪያ በወታደር ታጅቦ ለገበሬው እንዲደረስ ተደርጓል ሲሉ አስረደተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ግንባታ ተጀምሮ(ያዩ ማዳበሪያ ፉብሪካ)ቢሊዮን ብር ወጥቶበት መቅረቱ ይታወሳል።
ሜቴክ በምዕራብ ኦሮሚያ ያዩ አካባቢ የታቀደውን ያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውል የፈጸመው በ2004 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፋብሪካው በዓመት 3ዐዐ ሺሕ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ነበር።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments