top of page

መጋቢት 11፣2016 - የህዳሴ ግድብ 5 ተርባይኖች በመጪው ሳምንታት ሀይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተባለ


የህዳሴ ግድብ 5 ተርባይኖች በመጪው ሳምንታት ሀይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተባለ፡፡


ግንባታው ባይጠናቀቅም በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት ጀምሯል የተባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ፤ ተጨማሪ የሀይል አመንጪ ተርባይኖች ስራ እንዲጀምር እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


5 ተርባይኖችም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሀይል ማመንጭ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡


ይህንን ለሸገር የተናገሩት የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ናቸው፡፡


በአሁኑ ሰዓትም ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል እየተሸጠ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር አረጋዊ፤ ለታንዛኒያ እና ለደቡብ አፍሪካ ለመሸጥ ታቅዶ ንግግር ተጀምሯል ብለዋል፡፡


ለተገባደደው የግድቡ ስራ አሁን የሚቀሩት በአብዛኛውም ከውጭ የሚገቡ የመካኒካል እና ኤሌክትሪካል ግብአቶች ናቸው፤ አጠቃላይ ግንባታውም በ1 ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መገመቱንም ዋና ዳይሬክተሩ አውርተውናል፡፡


የህዳሴ ግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እስካሁን 18.9 ቢሊዮን ብር እንደሰበሰበም ተነግሯል፡፡


የህዝቡ ተሳትፎ በጎ የሚባል ቢሆንም አሁንም ድጋፍ እንዳይቀዘቅዝ የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አሳስበዋል፡፡


ከተጀመረ 13ኛ ዓመቱን የያዘው የህዳሴ ግድብ 95 ከመቶው ተጠናቋል የተባለ ሲሆን ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ 300,000,000 ዶላር እንደሚፈጅ መገመቱም ሰምተናል፡፡


የግድቡ ስራ በ2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page