top of page

መጋቢት 10 2017 - እርዳታን ለማይመለከተው ሰው ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረገ ግለሰብ እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጣ የሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ

  • sheger1021fm
  • Mar 19
  • 1 min read

የሰብአዊ እርዳታን ለራሱ ወይም ለማይመለከተው ሰው ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረገ ግለሰብ ከ10 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሚደነግገው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ፡፡


በስራ ላይ ያለው ብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አላስቻለም ተብሏል፡፡


አሁን በስራ ላይ ነው የተባለው ደንብ ኢትዮጵያ ተቀብላ ካፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች እና አሰራሮች ጋር የሚጣጣም አይደለም ተብሏል፡፡


በትናንትናው እለት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ እነዚህን ችግሮች የሚፈታ ድንገተኛ አደጋ ሲከሰትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የሰብአዊ እርዳታ ለተረጂዎች እንዳይደርስ ያደናቀፈ ወይም የከለከለ ሰው እስከ አስር ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሚደነግግ ነው፡፡


የሰብአዊ እርዳታን ለራሱ ወይም ለማይመለከተው ሰው ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረገ ግለሰብ የተዘረፈውን ንብረት ማስመለሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአስር እስከ ሃያ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና አንድ ሚሊዮን ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ያዛል፡፡


የሰብአዊ እርዳታን ድጋፍ ለማግኘት ሀሰተኛ መረጃ ወይም የተጋነነ ጥያቄ ያቀረበ፣ አደጋ ሳይኖር አደጋ እንዳለ አድርጎ የእርዳታ ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ከሶስት ዓመት በማያንስ እና ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ቀላል እስራት እና 15 ሺህ ብር እንዲቀጣ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ነው፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጠ….



ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page