top of page

መጋቢት 10 2017 - በጎዳና ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ደረት ላይ የሚንጠለጠል ፈቃድ ሊሰጣቸው ነው

  • sheger1021fm
  • Mar 19
  • 1 min read

በጎዳና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ነጋዴ የሚል ደረት ላይ የሚንጠለጠል ፈቃድ ሊሰጣቸው ነው፡፡


ህጋዊነታቸውን ተከትሎም የሚጠበቅባቸውን #ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል ተብሏል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆነን የንግድ ሥራ ለመምራትና ሥርዓት ለማስያዝ በሚል ባወጣው ደንብ ከዚህ ቀደም ህገወጥ ናችሁ ተብለው ይዋከቡ ለነበሩ ነጋዴዎች ፍቃድ እንዲሰጥ ደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት ማንኛውም በጎዳና ንግድ ላይ የተሰማራ ግለሰብ በሚሰራበት አቅራቢያ ባለ ወረዳ በመሄድ ተመዝግቦ ደረት ላይ የሚንጠለጠል ፍቃድ ማግኘት አለበት ተብሏል፡፡


በተጨማሪም በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ላይ የሚሰማራ ነጋዴ በዚህ ደንብ መሰረት ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት ያገኛል፡፡


የበጀት ዓመቱ ካበቃ በኋላ ባሉት 2 ወራት ጊዜ ውስጥም ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 30 ቀን ድረስ የግብር አስከፋይ መስሪያ ቤቱ ግብሩን ወስኖ እንዲከፍሉ ያደርጋል፡፡


የተሰጠውን ፍቃድ በየዓመቱ ማደስ እንደሚኖርበትና ከስራው ሲወጣም ለሰጠው አካል የመመለስ ግዴታ እንዳለበት ተቀምጧል፡፡


ይህ ደንብ ከየካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ተብሏል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page